tg-me.com/nibab_lehiwot/177
Last Update:
ጌታ ምን ላድርግልህ ቢለኝ ልቤን አሳይልኝ ነበር የምለው ልቤ ውስጥ ብገልጠው ያመኛል ብዬ የሸሸግኩት እልፍ ደብዳቤ ነበረ
ጌታዬ ሌላ ምን ላድርግልህ ቢለኝ ተንበርክኬ እሷን ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ ያልኩትን የምስጋና ፀሎት አሳይልኝ እለው ነበር
አሁንም ሌላ ምን ላድርግልህ ቢለኝ እሷ ያልነበረች ግዜ አረማመዴን እና ልቤ ውስጥ የተንከላወሰውን ሃሳብ አሳይልኝ እለው ነበር
እሱ ግን ምን ላደርግልህ ብሎ አይጠይቀኝም ...እኔ አድርግልኝ ብዬ ልጠይቀው ሳሰፈስፍ ስጣደፍ
ልጃቸው ሊሞትባቸው አኑርልኝ የሚሉ ፀላይ፣ ልጄ ሳያድግ አትግደለኝ የሚል አባት ፀሎት ፣ ፍትህ የሚሹ ብዚ ነብሶች ፣ ርሃብ ጠፍሮ ይዟቸው አንድ ጉርሻ ብትቸረኝ የሚሉትን
እውነታቸውን በገነዘብ የተቀሙ እልፍ ደካሞችንአምላክን በተማፅኖ የሚኖሩትን ሰዎች ወረፋ አስቀድማቸዋለሁ
የኔ ጥያቄ ቅንጦት ይሆን? እላለሁ
ምን አልባት ልባችን ላይ ያለው መሻት ቢመዘን እኩል ይሆን? ይሆናል ማን ያውቃል ?
የኔ ጥያቄ ከሌላው ጋር ሲስተያይ ቅንጦት ይመስለኛል ብዬ አስብና መሻቴን ገታለሁ🙃
✍Miraዥ
BY ሕይወትን - በገፅ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/177